Go to main content

ኦክራ (አቤልሞሹስ እስኩለንተስ (ኤል.)) መነሻው ኢትዮጵያ እንደሆነ የሚታመን ሲሆን በተለያዩ አገራዊ ቋንቋዎች በተለያዩ ስሞች ይጠራል፤ ቄንቄስ (አማርኛ)፣ ባሚያ (አረበኛ)፣ አሙላ (አኙዋክኛ)፣ ዋይካ (ጉምዝኛ) ወዘተ. በመባል ይታወቃል። የአለም አትክልት ማእከል(World Vegetable Center) ከሀገር ውስጥ አጋር አካላት ጋር በመሆን በምርትና ጥራታቸው የተረጋገጡ ሁለት የኦክራ ዝርያዎቸን በማስተዋወቅና በማሰራጨት ላይ ይገኛል። ዝርያዎቹም ቄንቄስና ዋይካ ይባላሉ። ኦክራ ከፍተኛ የንጥረ ነገር ይዘት ስላለው ቅጠሉ፣ እንቡጥ፣ አበባው፣ ግንዱ፣ ለጋ ፍሬው እና ዘሩ ታሳቢ ተርጎ ይመረታል ቀጥታ ለምግብነት ወይም ለመድሃኒትነት ይውላል። የካርቦሃይድሬት፣ ፋይበር፣ ማዕድናት (ካልሲየም፣ ፎስፎረስ፣ ፖታሲየም፣ ማግኒዚየም እና ብረት)፣ ቫይታሚን (B1፣ B2፣ B6፣ C፣ K) እና አንቲኦክሲደንትስ ምንጭ ሲሆን ይህም ኦክራን ጤናማ ምግብ ያደርገዋል። ቅጠሉና ለጋ ፍሬው በተለምዶ አትክልት (ሳላድ)፣ ሾርባ እና ወጥ ውስጥ ይጨመራሉ። የኦክራ ፍሬ ከቦካ ኮምጣጤ ለመስራት ያስችላል። አበባውና እንቡጥ የቅጠል ቀንበጦች እንደአትክልት ለምግብነት ይውላሉ። የኦክራ ዘር ደግሞ ተቆልቶ፣ ወደዱቄትነት ተፈጭቶ ቡናን ተክቶ ይጠጣል። በተጨማሪም ኦክራ ለመድኃኒትነት ጥቅም ላይ ይውላል, ለምሳሌ ቁስለትን ለማከም።

Metric
From
To
Interval
Export
Download Full History